አጫጭር ዜናዎች

በኩዌት የትዊተር ዘለፋ ሊያስገድል!

ነቢዩ  መሐመድን  በትዊትር ላይ  ዘለፈክ  ተብሎ የኩዌት ሰው  ሊገደል ነው

በብዙ የሱኒ እስላሞች ዘንድ የሚከበረውን የሻርያ ህግን  መሰረት በማድረግ የኩዌት ባለስልጣናት አንድን የኩዌቲ ተወላጅ ሰው በትዊትር ላይ ነቢዩ መሐመድን ዘለፈሃል በማለት አስረውታል። ይህ ሁኔታ በሰውየው ላይ ሞት ይገባዋል የሚል ጥሪ አስከትሏል።

የኩዌት የአገር ውስጥ አስተዳደር በመንግስት ዜና ማሰራጫ (KUNA) ላይ የሰውየውን ማንነት ሳይገለጽ “አንድ ሰው የእስላምን ሃይማኖት አንዳዋረደ ነቢዩ መሐመድን፣ ተባባሪዎቹንና ሚስቱን ዘለፈ” በማለት ነበር ያወጣው። ሰውየው የሰጠው እስታየት ምን እንደሆነ ወዲያውኑ ግልፅ ባይደረግም፤ የአገር ውስጥ አስተዳደር በጉዳዩ እንዳዘነ ገልፆ፤  ማህበራዊ የቴክኖሎጂ የግንኙነት አውታሮችን ያለአግባብ  በመጠቀም የእስልምናን መስረታዊና መንፈሳዊ እሴቶች የሚያዋርዱትን «አንዳንድ ገለሰቦች» ያለ ምንም ምህረት እንደሚፋረዳቸውና ይህንንም ዓይነት «ከባድ ወንጀሎች» እንደሚዋጋቸው ገልጿል ።

ግለሰቡ በዜና ዘገባዎች ላይ ማንነቱን ሳይገለጽ «እኔ ፈጽሞ ቅዱሱን ነቢይ አልዘለፍኩም» በማለት ክሱን አጣጥሏል። በመቀጠልም እሱ ሳያውቅ ሌላ ስው በእሱ ስም አስተያየት እንደጻፈ ተናግሮአል። ግለሰቡ በምርመራ ላይ እንደሆነና  ፍርድ እየተጠባበቀ መሆኑም ተዘግቧል።

ኩዌት ብዙውን ጊዜ “ስድበ መለኮትን” ወይንም ሃይማኖትን አርክሰሃል የሚል ወንጅልን እንደ ጎረቤት ሳይዲ አረቢያ በሞት ባትቀጣም እስር ግን አይቀሬ ነው፤ በሳውዲ አረቢያ ነቢዩ መሐመድን በትዊተር ላይ ዘለፍሃል ተብሎ የተከሰሰ ጋዜጠኛ ሞት ይገባዋል የሚል ጩኸትን አስከትሏል።

ደሩ ግን ብዙ የኩዌቲ የፓርላማ አባላት ወንጀለኛው እንዲገደል ጥሪ ሲያቀርቡ፤ መንግስታቸው በወንጀለኛው ላይ የሞት ፍርድ ካላስተላለፈ ህዝቡ በገዛ ራሱ እጅ ፍርዱን እንደሚሰጥ አንዳንዶቹ አስተያየት መስጠታቸውን የአረብ ታይምስ ዘግቧል።

«ይህ ጥቃት በቅዱሱ ነቢዩ፣ የአማኞች ሁሉ እናት በሆነችው --- በሚስቱ እና በተባባሪዎቹ ላይ ስለሆነ (ከአገር ውስጥ አስተዳደር) አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ እንጠይቃለን» ሲል አንድ የፓርላማ አባል ተደምጧል።

በ2009 አንድ የልዩ ጦር መኮንን ነቢዩ መሐመድን ዘለፍሃል ተብሎ ከተያዘ በኋላ ለ6 ወር እንደታሰረ ተዘግቦአል።

በ2005 የከፍተኛው ፍርድ ቤት አንድን ጋዜጠኛ በ2004 ባወጣው ጽሑፍ ላይ ቁርአንን አዋርደሃል በማለት ለአንድ አመት ከስራ እንዳገደውና አሳታሚውን 170 ዶላር መቅጣቱን የአሜሪካ ስቴት ድፓርትመንት ጠቅሶ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የደረሰው ሶስት የእስልምና ተሟጋቾች ባቀረቡት አቤቱታ መሆኑንም ጨምሮ ዘግቧል።

በእስልምናና በሙስሊሞች ላይ በማንኛውም መንገድ የሚደረጉ ዘለፋዎችን እንዲሁም ሃይማኖቱን መቀየርን የሚከለክለውና እጅግ በጣም አወዛጋቢ የሆነው የሻሪያ የሕግ ኮድ፤ ማለትም የሃይማኖት ስድብ ህጎች (ብላስፌሚ ሎውስ) የተመሰረተው በቁርአን ትምህርት ላይ ነው፡፡ አናሳ ሃይማኖቶችን፣ ምሁራንንና ጋዜጠኞችን ለማጥቃት የሻሪያ አንቀጾችን እንደ ፓለቲካ መሳሪያ መጠቀም በጣም የታወቀ አሰራር ነው።

«ሃይማኖትን ያዋረደ ጋዜጠኛ እስር እንደሚገባው ህጉ ይጠይቃል» አለም አቀፍ የሃይማኖት ነጻነት የ2005 ሪፓርት ዘግቧል። የምሁራን ነጻነት በተግባር ራስን በራስ በማቀብ ላይ ነው፤ ምሁራኑም ልክ እንደ ጋዜጠኞቹ ሁሉ እስላምናን ከመተቸት በሕግ የተከለከሉ ናቸው፡፡ ማንኛውም አንድ ጸሐፌ እስላምን፣ የገዢዉን ቤተሰብ ወይም የህዝብን ሞራል የሚጐዳ ነገር ጽፏል ብሎ አንድ የሙስሊም ዜጋ ካመነ ህጉ የመክሰስ መብት ይሰጠዋል።

ሃይማኖት የመሳደብ ህጎች (ብላስፌሚ ሎውስ) በቅርብ ዘመናት እየገነኑ መጥተዋል፤ በመካከለኛው ምስራቅ አልፎ አልፎ ደግሞ በምእራቡ ላይ በመናገር ነፃነት፣ በሰብአዊ መብቶች፤  እንዲሁም በሃይማኖት ነፃነት ላይ ከፍተኛ ጥቃት እያንዣበበ ነው በማለት አንዳንድ በዚህ መስክ እውቀት ያላቸው ሰዎች ይከራከራሉ። ሌሎች ደግሞ በሙስሊሙ ዓለም የእስልምና ህግ በፈላጭ ቆራጭ መንግስታትና በአክራሪ ሃይሎች ስልጣንን ለመያዣና በስልጣን ላይ ለመቆያ በክፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሙበት እንጂ ሃይማኖታዊ  ምክንያት እንዳልሆነ ይከራከራሉ።

ምንጭ-የክርስቲያን ፓስት  ማርች 28, 2012; Kuwaiti Man Threatened With Death for 'Offending' Prophet Muhammad on Twitter

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

በኩዌቱ ሰው ትዊተር ድረ ገፅ ላይ የቀረበው ትችት ይዘት ምን እንደሆነ ባይታወቅም፣ ትችቱን አቅርቧል የተባለው ሰው ግን ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ለመኖሩ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የኩዌት መንግስት ካለው የላላ ፖሊሲ አኳያ እንኳን ሰውየው ከመገደል ቢድን ሕዝቡ እራሱ እንደሚገድለው ግልፅ የሆነ ማስፈራሪያ ተቀምጧል፡፡

እንደዚህ ዓይነት ነገሮች በሙስሊም አገሮች ውስጥ መደረጋቸው ለምንድነው? ሰዎች ስለ ሃይማኖታቸው ሐሳባቸውን ለመግለፅ ስለምን መብት አይኖራቸውም? አንድ ሃይማኖት እና የሃይማኖት መሪዎችና ቤተሰቦች ትችትን ስለምን ይፈራሉ? እነዚህን ጥያቄዎች ለሙስሊም አንባቢዎቻችን በማቅረብና እንዲያስቡበት እንፈልጋለን፡፡ በእርግጥ እስልምና እንደ ሃይማኖት ለሰዎች ልጆች መብትና ሰላም የቆመ ሃይማኖት ነውን?

አንድ ሃይማኖት ትችትን የሚቃወም እንዲያውም የሚቀጣ ከሆነ፣ ውስጣዊ ችግር ያለበት መሆኑን አይጠቁመንምን? ምናልባትም ሃይማኖቱ እራሱን መመከት ስለማይችል ሰዎች ሁሉ ያለምንም ተቃውሞ እንዲቀበሉት ማድረጊያ ዘዴው ይሆንን? በአሁኑ ጊዜም ሆነ በጥንት እየተደረገ እንዳለው ክርስትና እምነት ግን ትችትን አይፈራም፡፡ ለቀረቡት ትችቶች ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ ሎጂካዊ መልሶች አሉት፡፡ ከዚህም በላይ የእምነቱ መሰረት እግዚአብሔር እራሱ ስለ እራሱ በተቃዋሚዎች እና በተሳዳቢዎች ላይ ፍርዱን ይሰጣል፡፡

የክርስትና እምነት መርሆዎች ለምዕራቡ ዓለም ሰላማዊና ኑሮ የሰብዓዊ መብት መከበር መሰረትን የሰጡት፡፡

የዚህ ድረ ገፅ አዘጋጆች በአጫጭር ዜናዎች አማካኝነት በሙስሊሙ ዓለም ምን እየሆነ እንዳለ እያቀረቡ ሙስሊሞችና ሌሎች አንባቢዎች ለገዛ እራሳቸው ሕይወት በአግባቡ እንዲያስቡና የሰላምና የነፃነት መሰረት ከሆነው ከእግዚአብሔር ጋር በክርስቶስ በኩል የመታረቂያን መንገድ እንዲጨብጡ እንመክራለን፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ አሜን፡፡

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ