የአንድ አፍሪካዊው የሚረብሹ ጥያቄዎች፡ በእስልምና ላይ!

በBrother Banda

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

በተለያዩ አገሮች ውስጥ ፀረ ጥቁሮች የሆኑ ብዙ ዘረኝነቶች እንዳሉ እውነት ነው፡፡ እንዲሁም አንዳንድ ቤተክርስትያናትና እውነቱ የተምታታባቸው ክርስትያኖች ፀረ ጥቁሮችና ፀረ ድሃዎች አመለካከት ያላቸው የሌሎች ሰዎች ተፅዕኖ እንዲቀርፃቸው በአሳዛኝ ሁኔታ አድርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ድሃዎችንና እንግዶችን እንዲሁም ምንም መጠጊያና መከላከያ የሌላቸውን የሌላ አገር ተወላጆችንም እንድንወድ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም እንኳን እራሱ በአፍሪካ ውስጥ የተሰደደ ሕፃን ነበረ (ማቴዎስ 1-2)፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሱን ክርስትና ከፀረ ጥቁር ዘረኝነት ጋር ማመሳሰል በጭራሽ አይገባም፡፡ ነቢዩ ሙሴ አፍሪካዊትን እንዳገባና በዚህም የተነሳ በዘረኝነት በእሱ ላይ ተነስታ በነበረችው በሙሴ እህት በማርያም ላይ እግዚአብሔር እንደተቆጣ ማስታዎስ አለብን፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር በለምፅ ለሰባት ቀናት ያህል ቀጥቷት ነበር (ዘኁልቁ 12)፡፡ የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ዘረኝነትን ይጠላል፡፡ ቁርአን ስለ ዘረኝነት እና ዘርን በተመለከተ ስለሚኖር ጭቆና ለመሆኑ ምን ይላል የሚለውን አንስቶ መነጋገር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ብዙ ጥቁሮችና የሌላ አገር ተወላጆች እስልምና ውስጥ ሲገቡ፣ እስልምና ከዘርና ከዘረኝነት ንፁህ የሆነ ሃይማኖት አድረገው ሲቆጥሩትና ሲናገሩለት እንመለከታለን፡፡

ይሁን እንጂ በቁርአንና በእስልምና ታሪክ ውስጥ በጣም የሚረብሹ ነገሮችን መመልከት እንችላለን፡፡ እኔንም ጸሐፊውን ያስደነቀኝ ነገር በምዕራቡ ዓለም የሚኖሩ ጥቁሮች እስልምናን ከዘረኝነት የጠራ አድርገው እስልምና ውስጥ ዘለው መግባታቸው ነው፡፡  

ጥያቄ አንድ፡ የሙስሊሞችን ቁርአን በተመለከተ የሚረብሽ ጥያቄ

ለምሳሌ የሙስሊሞችን ቅዱስ መጽሐፍ ቁርዓን የሚለውን የሚከተለውን ተመልከቱ፡- ‹ፊቶች የሚያበሩበትን (ነጭ የሚሆኑበትን) ፊቶችም የሚጠቁሩበትን ቀን (አስታውስ) እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን? ትክዱት በነበራችሁት ነገር ቅጣታችሁን ቅመሱ፡፡ (ይባላሉ)፡፡ እነዚያማ ፊቶቻቸው ያበሩትማ በአላህ ችሮታ (ገነት) ውስጥ ናቸው እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ 3.106-107፡፡

እኔ እዚህ ጋ እንደ አንድ ጥቁር አፍሪካዊ ወይንም ሰው የምጠይቀው ጥያቄ ነጭነት (በአማርኛ የሚያበራ ፊት) ተብሎ የተባለው ከመልካም ስራ ጋር ሲያያዝ ጥቁርነት ደግሞ ከክፉ ስራ ጋር ለምን እንደተመሳሰለ ነው፡፡

ጥያቄ ሁለት፡ የሙስሊሞችን ቁርአን በተመለከተ የሚረብሽ ጥያቄ

ልክ እንደ አንድ አፍሪካዊ እኔም እራሴ የአፍሪካን ሕዝብ ታሪክ በተመለከተ ሙስሊሞች ስላላቸው ሚዛን ያጣ የምርምር ውጤት እጅግ በጣም ግራ ተጋብቻለሁ፡፡  

በሰሜን አፍሪካ እኛ የምናውቀው የሞሮኮ የሊቢያ የአልጀሪያ እና ግብፅ እስከ ሱዳንና ኢትዮጵያ ድረስ ክርስትያኖች ነበሩ፤ ይህም እስልምና ገብቶ አጥቢያ ቤተክርስትያናትን ጨርሶ እስካወደመ ድረስ የሆነ ነገር ነበር፡፡ ይህንን የክርስትያን ቤተክርስትያኖችን ውድመት ታሪክ በእስልምና ስነ ጽሑፍ ላይ ለምን አላገኘነውም?

እንደገናም የሚከተለውን አስተውሉ፡ አፍሪካ እንደ አግሰቲኖ ሂፖ (አልጀሪያ)፣ ክሌመንት እና አትናዌዎስ ግብፅ እና ቴርቱሊያን የካርቴጅ (የአሁኑ ቱኒዝ) የመሳሰሉ ታላላቅ የክርስትያን ፈላስፋዎችና አስተማሪዎች ነበሯት፤ ኢትዮጵያ ደግሞ ከዩሮፕ ፍፁም ልዩ የሆነ እራሱን የቻለ አፍሪካዊ የመጀመሪያ የክርስትና አገር ናት (ሐዋርያት 8)፡፡ በእርግጥ በብሪቴን፣ በካናዳ እና በአሜሪካ ወይንም በስፔን ወይንም በሌላ የምዕራብ አገሮች ውስጥ ቤተከርስትያን ሳይመሰረት በመጀመሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ አጥቢያ ቤተክርስትያን የመመስረቱን ታሪክ ማየቴ በጣም አስደናቂ ሆኖ አግኝቸዋለሁኝ፡፡ ነገር ግን ስለዚህም ለምንድነው ዛሬ የእነዚህን አፍሪካዊ ቤተክርስትያናት ታሪክና የማንሰማው ደግሞስ የእነርሱን ታሪካዊ ቅሬት የማናየው ለምንድን ነው?

ምናልባትም ይህንን ፍንጭ ለማግኘት ወደ ቁርአን ውስጥ መግባት ሊኖርብን ይገባን ይሆናል፡፡ በቁርአን 9.5 ላይ ያለውን የሚከተለውን ቁጥር ተመልከቱ፡ ‹የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሏቸው ያዙዋቸውም ክበቡዋቸውም ለነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ ቢፀፀቱም ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ ግዴታ ምፅዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና›፡፡ ይህም የእራሳቸውን እምነት ለመከተል የሚመርጡትን በተመለከተ እስልምና ያለውን አጠቃላይ መርሆ ያሳያል፣ ይህም ሐሳብ በቁርአን 3.28 ላይ እንደሚከተለው የበለጠ ተብራርቷል፡- ‹ምዕምናን ከሐዲዎችን ከምእምናን ሌላ ረዳቶች አድርገው አይያዙ ይኽንንም የሚሠራ ሰው ከአላህ (ሃይማኖት) በምንም ውስጥ አይደለም ከነርሱ መጠበቅን ብትጠበቁ እንጂ አላህም ነፍሱን (ቁጣውን) ያስጠነቅቃችኋለው፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡›

የሱዳን ታሪክ ለዚህ ነጥብ ጥሩ ማስረጃ ነው፡፡ ሙስሊሞች በግብፅ እስላማዊ ማመሉኮች አማካኝነት ሱዳንን ከመውረራቸው 1275 ዓ.ም በፊት፣ ሱዳን ሦስት ትናንሽ ክርስትያናዊ መንግስት ነበራት እነሱም የሚታወቁት፡-

ኖባትያ ፡- በሰሜን ስትሆን የኩስቱል ዋና ከተማ ነበረች፡፡

ማኩሪያ፡- የጥንቱ ዶንጎላ ዋና ከተማ የነበረች ስትሆን፤

አሎዲያ ወይንም አልዋ፣ የ የሶባ ዋና ከተማ ነበረች፡፡

እነዚህ ሦስቱ የክርስትያን አገሮች ከ 300 እስከ 1500 ዓ.ም ድረስ የራሳቸው የሆነ የጽሐፍ ቋንቋ፣ ታላላቅ የትምህርት ማዕከላት፣ ዓለም አቀፍ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ ከግብፅ ከኢትዮጵያና ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር  የነበራቸው ሲሆን፣ ወደ ሌሎቹ የአፍሪካ አገሮች ሚሽነሪዎችንም ልከው ነበር፡፡ (see K. Milhalowski,Faras, vol.2, Poland, 1965 for extensive archaeological and historical documentation on these states).

ኢብን ሳሊም አል-አሷኒ የተባለው አረብ እንኳን ሶባን ባየ ጊዜ በጣም ተደንቆ ያላትን ነገር እንደሚከተለው ገልጦታል -- ‹ወደብ ግንባታዎች፣ ሰፋፊ አዳራሽ ያላቸው ቤቶች፣ ቤተክርስትያናት እና ምድሩ ደግሞ ከማኩሪያ ይልቅ ምርታማ ነው (እንዲሁም አላቸው) ብዙ ስጋ እና ጥሩ፤ ጥሩ ፈረሶች፡፡

ነገር ግን ይህ ሁሉ የወደመው በ1275 በተደረግ የሙስሊም ወራሪዎች እንጂ በዮሮፕያውያን ቅኝ ገዢዎች አልነበረም፡፡ ተመሳሳይም የሆነ ልክ የሌለው ውድመት በአፍሪካ ሁሉ ውስጥ በሙሉ ተከናውኗል ነገር ግን ማንም ሰው ለዚህ ሁሉ ወድመትና ጥፋት ሙስሊሞችን ተጠያቂ ሲያደርግ አንመለከትም፡፡ ነገር ግን ለምን? የሙስሊም አረቦች ዘረኝነት ልክ እንደ ሮፕያኑ እጅግ ክፉ የሆነ ዘረኝነት ነው፣ ስለዚህም ጥያቄው አሁንም እንዲቀጥል የሚፈቀድለት ለምንድነው? የሚለው ነው፡፡

ምክንያቱም አሁንም እየቀጠለ ነው፡፡ በ1990ዎቹ በሱዳን ሰሜን ምስራቅ አፍሪካ በሙስሊሞች የጅሃድ ጦርነትን አማካኝነት አፍሪካውያን እየተሰቃዩ ነው፤ በዚያም እጅግ ብዙ ሺ የሚሆኑ ክርስትያኖችና የማያምኑት ተገድለዋል ብዙዎቹም በስቅላት ተገድለዋል፡፡፡፡ ሌሎች ደግሞ እጅና እግራቸው በተለዋዋጭ ጎን እየተቆረጠ እንዲሰቃዩ ተደርገዋል ማለትም የቀኝ እጅ እና የግራ እግር ወይንም የግራ እጅና የቀኝ እግር፡፡ በቁርአን 5.33 ላይ የምናነበው የሚከተለው ቃል ‹የነዚያን አላህንና መልክተኛውን የሚዋጉ በምድርም ላይ ለማጥፋት የሚተጉ ሰዎች ቅጣት (1) መገደል ወይንም (2) መሰቀል ወይንም (3) እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በማፈራረቅ መቁረጥ ወይንም (4) ከአገር መባረር ነው፡፡ ይህ ለነሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት ነው በመጨረሻይቱም ለእነርሱ ከባድ ቅጣት አላቸው፡፡› ስለዚህም የሆነው ነገር ሁሉ ከሱዳን ልምምድ ጋር ሲታይ ዝም ብሎ አጋጣሚ ክስተት ነውን?

ይህ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ እየተካሄደ እያለ የሙስሊም አገሮች የካርቱን መንግስት ይህን ተግባር እንዲያቆም አንድም ጊዜ ተናግረው አያውቁም፡፡ ለመሆኑ ለምንድነው ዝምታው? ነገር ግን በደቡብ አፍሪካ ስለነበረው የአፓርታይድ አገዛዝ ብዙ ጩኸት ነበረ፡፡ ለምንድነው ይህ ሁለት ዓይነት አቋም በሙስሊም አገሮች የተወሰደው?     

ጥያቄ ሦስት፡ በሙስሊሞች ባሪያ መደረግን በተመለከተ የሚረብሽ ጥያቄ

ከዚህ በላይ ያለው ታሪክ ደግሞ እኔን ወደ ባርነት ጥያቄ ያመጣኛል፡፡ ሙስሊሞች እንደሚሉት ከሆነ ሰዎችን ባሪያ ማድረግ የክርስትያኖች ስራ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን የባሪያ ንግድን የብሪቲሽ መንግስት ለማስወገድ ሲነሳ ዋናውን ሚና የተጫወቱት ክርስትያኖች ነበሩ ከእነዚህም ውስጥ የሚጠቀሱት ዲቪድ ሊቭንግስቶንና ዊልያም ዊልበርፎርስ አሉበት፡፡ አረብ ሙስሊሞች ግን አፍሪካውያንን ባሪያዎች ያደርጉ ነበር፤ (ይህም አላህ በቁርአን 4.24-25 ላይ በገባው ቃል ኪዳንን በመከተል ነበር፡፡) በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ስላሉት ደሴቶች ስለ ዛንዚባርና ፔምቤ በ 19ኛው ሞተ ክፍለ ዘመን ስለሆነው ነገር የተጻፈውን አላነበባችሁምን? ወይንም ደግሞ የባሪያ ንግድንና ስርዓትን በማስወገዱ ታሪካዊ ክስተት ላይ አንድም የሙስሊም አገር አለመሳተፉ እናንተን አላስደነቃችሁምን?

ታሪኩን በግልጥ ላስቀምጠው፡፡ ዩሮፓውያን በባሪያ ንግድ ላይ  ለጥቂት መቶ ዓመታት የተሳተፉ ቢሆንም የአፍሪካውያን የባሪያ ንግድ ግን ከዮሮፓውያን ተሳትፎ አንድ ሺ ዓመት በፊት ቀድሞ የተመሰረተ የታሪክ እውነታ ነው፡፡

አፍሪካውያንን ባሪያ የማድረግንና የመውረርን ልምድ በክርስትያን ዮሮፕ በር ላይ የተፈፀመ አስፀያፊ ስራ ነው የሚለው የሙስሊሞች ውንጀላ በጭራሽ በታሪክ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም፡፡ የሮማውያንም ሆኑ የግሪክ መንግስታት ሁለቱም ባሪያ አድራጊ መንግስታት ነበሩ፣ ነገር ግን የእነርሱ ባሪያዎች ብዙዎቹ ‹ካውካሲያን› ነጮች ነበሩ፡፡ በእርግጥ በእንግሊዝናው ባሪያ የሚለው ቃል “ስሌቭ የመጣው ከስላቪክ ጅማሬ ነው፡፡ ሮበርት ሂዩስ በጻፈውና Fraying of America በሚለውና በየካቲት 1992 በታይም ጋዜጣ ላይ በወጣው ጽሑፉ ውስጥ ይህንን የተሳሳተ አመለካከት እንደሚከተለው አርሞታል፡-

“እንደሚታወቀው የአፍሪካ የባሪያ ንግድ ማለትም የጥቁሮችን ማጓጓዝ የአረቦች ፈጠራ ነበር፣ እርሱም የዳበረው ጉጉት ባላቸው ነጋዴዎች ከአፍሪካውያን ጋር በመተባበር ነበር፡፡ ይህም ተዋቅሮ የነበረው እጅግ በጣም እረፍት ባልነበረው አረመኔነት ጋር ተያይዞ ነበር፣ ይህም ነጭ ሰው በአፍሪካ ምድር ላይ ከመርገጡ ብዙ መቶ ዓመታት በፊት ሲሆን በሰሜን አሜሪካ የባሪያ ንግድ በመጨረሻ እስከ ተደመሰሰ ድረስ ነበር፡፡ በነቢዩ መሐመድ ጽሑፍ ውስጥ ባርነትን የሚከለክል ምንም ነገር የለም፣ ስለዚህም ነው የባሪያ ንግድ ስራ የአረብ ተፅዕኖ ያለበት ስራ የነበረው፡፡ እንዲሁም ደግሞ የአፍሪካ የጎሳ መሪዎች ባይተባበሩበት ኖሮ የባሪያ ንግዱ እውነት ሊሆን አይችልም ነበር፡፡ እነርሱም እርህራሄ በሌለው ጦርነቶቻቸው ምርኮኞችን ያቀርቡ ነበርና የእነርሱ ትብብር በጣም አስፈልጓል፡፡  እንደ Roots ዓይነት የአሁኑ ጊዜያት ብቅ ያለው የታሪክ ልብ ወለዶች ላይ የቀረበው ስዕል ባሪያ አድራጊ ነጮች ሳንጃና ጠመንጃ ይዘው በሰላም በሚኖሩና፣ በአፍሪካውያን የተከማቹ መንደሮች ተሰማሩ የሚለው ነገር ከታሪካዊ መረጃ እጅግ በጣም የራቀ ነው፡፡ የባሪያ ንግድ ስነ ዘዴው ለዘመናት በቦታው ላይ ነበር፤ ምንጩ ደግሞ በአፍሪካውያን ቁጥጥር ስር ነበር፡፡ እንዲሁም ሁኔታው በባሪያ ንግድ ከጠፋ በኋላ እንኳን በቀላሉ አላቆመም ነር፡፡ ለአረብ ኤሜሬቶች የባሪያ ገበያዎች ምንጭ የነበሩት ማዕካለት በጂቡት ውስጥ በ1950ዎቹም ውስጥ እንዲሁም በ1960 ድረስ ክፍትሆነው ይሰሩ ነበር፡፡ በሞሪታኒያና በሱዳን ውስጥም የባሪያ ንግድ እጅግ በጣም አብቦ ነበር፡፡ አሁንም እንኳን በሩዋንዳና በናይጀር ውስጥ የባሪያ ባለቤትነት እንዳለ መረጃዎች አሉ”

በአንዳንድ ሙስሊሞች የሚቀርበውና ባርነት አፍሪካውያንን ወደ እስልምና ለመቀየር የእግዚአብሔር አንድ መንገድ ነው የሚለው ክርክር፤ አንዳንድ ክርስትያኖች በተሳሳተ መንገድ ከሚሉትና አፍሪካውያን በ19ኛው መቶ ወደ አሜሪካ መምጣታቸው የወንጌልን መልእክት እንዲሰሙ መንገድ ከፍቶላቸዋል ከሚለው አባባል ተመሳሳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህ ዓይነቱ ክርክር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም ዓይነት ድጋፍ በፍፁም የሌለው ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህርይ ክብርን የማይሰጥ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ ግን እስልምና እስካሁን ድረስ ከታሪክ ምንም ትምህርትን አልወሰደም፤ በእስላም ማዕከላዊ አገሮች ውስጥ፤ እንደ ሳውዲ አረቢያ ባሉት፤ አሁንም እንኳን የሌላ አገር ሰዎች ባሪያዎች ሆነው ይገኛሉና፡፡ (የዩናይትድ ኔሽን የባሪያ መረጃ 1994፡፡)   

ጥያቄ አራት፡ የሙስሊሞችን ባህል በተመለከተ የሚረብሽ ጥያቄ

ሙስሊሞች እንደሚሉት ከሆነ የምዕራባውያን ክርስትያኖች አፍሪካን መቆጣጠር ይመኛሉ ነው፡፡ ነገር ግን እኛ አፍሪካውያን የምዕራባውያንን የኮካኮላ ልማድ የማንወስደውና ነገር ግን የሰባተኛውን መቶ ዓመት የአረብ ልብስ (ጀለቢያ) ባህል እንድንወስድ የምንገደደው ለምንድነው? በኔ አፍሪካዊ የባህል አለባበስ ውስጥ ምን ስህተት ወይንም ችግር ተገኝቶበታል? ጥቁር አፍሪካውያን ከቶ ለምንድነው ወደ አረቡ ከተማ መካ ከተማ ፊታቸውን አዙረው መፀለይ የሚገደዱት ለምንድነው? ማነው ማንን የሚያስገድደው? ለምንድነው የአገር ከተማዎችን ወደ አዲስ አበባን ወደ ናይሮቢን ወይንም ወደ ሉሳካ ፊት አዙሮ ለምን አይፀልይም? እኔ እንደማስበው እግዚአብሔር የትም ቦታ ይገኛል እንደዚሁም ፀሎት መቅረብ ያለበት በቀጥታ ወደ እርሱ ነው እርሱ ደግሞ ከምድር በላይና የሚኖረው በሰማይ ነው፡፡ እውነት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አንድ ጊዜ የተናገረውን ነገር አስታውሱ እኔ ከሰማይ ነኝ እናንተ ግን ከምድር ናቸሁ አለ፡፡

ከዚህም በላይ እኛ የእርሱን ቃል በአረብኛ ብቻ ማንበብና መናገር የምንገደደው ስለምንድነው? እግዚአብሔር የሚናገረው አረብኛን ቋንቋ ብቻ ነውን? እርሱ የእኔን አፍሪካዊ ቋንቋ መረዳት ችሎታ የለውም ማለት ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ አሁን በዓለም በሚኖሩና ከ2000 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በመተርጎሙና በመነበቡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ ምክንያቱም የእኔ እግዚአብሔር የሁሉንም ቋንቋዎች መናገር እንደሚችል አውቃለሁና ይህ ለእርሱ ምንም ችግር አይደለም፡፡

መደምደሚያ

ይህ ደብዳቤ የተጻፈው ከፍቅር በመነጨ ልብ ነው - ማለትም ለእውነት ካለ ፍቅር የተነሳ ነው፣ ምንም እንኳን ቢጎዳ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን እኛ አፍሪካውያን የራሳችን የሆነ ታላቅ አፍሪካዊ ቅርስ እንዳለን ነው፣ ይህም ታሪካችን አንዳንዴ ሲወሰድብን ኖሯል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የእኛ ፈጣሪ ነው እርሱም እኛን ልክ ሰዎች እንደሆንን ነው የሚያውቀው፡፡ ከዚህም በላይ አዳምና ሔዋንን የአፍሪካ ሕዝቦች የመጀመሪያዎች ወላጆች እርሱ አድርጓቸዋል፡፡

እንዲሁም ደግሞ አፍሪካን ለሌላ ዓላማ እግዚአብሔር ተጠቅሞባታል አፍሪካዊቷን ግብፅ ለአይሁድ ሕዝቦች መጠጊያ በማድረግ በዮሴፍ ታሪክ ወቅት (ዘፍጥረት 39-50፡፡) እንዲሁም እግዚአብሔር የሰውን ስጋ ለብሶ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሲሆን የተሰደደው በአፍሪካ አገር በግብፅና የተወሰነውን ልጅነቱን ያሳለፈውም ሌላዋ የአፍሪካ አገር ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያም እስልምና ከመጀመሩ ብዙ መቶ ዓመታት በፊት በራሷ ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስ የነበራት አገር ናት፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በወደፊቱ የመንግስተ ሰማይ ውስጥ የብዙ አገር ሰዎች እንደሚኖሩ ተነግሮናል ይህም የሚጨምረው አፍሪካውያንን ነው (ራዕይ 21.24፡፡) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ሰዎች ሁሉ ከቋንቋ ከነገድ እና ከመንግስታት ሁሉ ውስጥ በክርስቶስ ኢየሱስ በፈሰሰው ደም ከኃጢአታቸው ነፃ መውጣት እንደሚችሉ ነው፡፡ ምክንያቱም እርሱ ለሰዎች መዳን መስዋዕት ሆኖ ሞቶ፣ ለኃጢአታቸው ዋጋን ከፍሎ ከሞት ተነስቷልና፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሱ አምላክ ከቁርአኑ አምላክ የተለየ ስለሆነም በእርሱ ስም አማኞቹ ሰዎችን እንዲገድሉለት ወይንም ደግሞ በጦርነት ማርከው ባሪያዎችና እንደፈለጉት የሚጠቀሙባቸው ንብረት እንዲያደርጓቸው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮቹን በፍፁም አላዘዛቸውም፡፡ እያንዳንዱ ሰው እርሱን ለመከተል ወይንም ላለመከተል መብት አለው፤ እርሱን የማመንና የመከተል እድል ተሰጥቶታል እንጂ ግዴት የለበትም፡፡ እግዚአብሔር መሐሪ መሆኑን አውቀው የጌታ ኢየሱስን ስም በመጥራት ወደ ራሱ የሚመጡትን እግዚአብሔር እንደሚያድናቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁሉ የምናነበው ነገር ነው፡፡

ይህ ደግሞ በትንቢተ ኤርምያስ 38-40 ላይ ያለውን ኢትዮጵያዊ እንዲሁም ደግሞ በሐዋርያት ስራ 8 ላይ የተጠቀሰውን ኢትዮጵያዊንም ይጨምራል፤ ይህንን ጽሑፍ የጻፍኩትም አፍሪካዊን እኔንም ይጨምራል፤ እናንተም በጌታ በኢየሰስ በኩል በተገለጠው ምህረት በኩል ወደ እግዚአብሔር ብትመጡ በምህረቱ ውስጥ እንደምትጨመሩ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ እኔ የራሴን ጥያቄ ጠይቄአለሁ አሁን ተራው የእናንተ ነው እናንተም የራሳችሁን ጥያቄ ጠይቁ፡፡ እንደ አንድ አፍሪካዊ እኔን በእርግጥ የረዳኝ ማነው? እንደ አንድ አፍሪካዊ ለዘላለም ሕይወቴ እኔን በእርግጥ የሚረዳኝ እውነት ላይም የሚያቆመኝ ክርስትና ነው ወይንስ እስልምና? ብላችሁ  በማስተዋል ጠይቁ ከዚያም በማስተዋልና በጥንቃቄ የምትይዙትን ምረጡ፤ ምክንያቱም የእናንተ ሕይወት የሚመሰረተው በዚህ ምርጫ ላይ ነውና፡፡

 

የትርጉም ምንጭ: An African Asks Some Disturbing Questions of Islam

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ