ሴቶች ቦታ በንፁህ እስልምና

ክፍል አንድ - የወንዶች የበላይነት

[ክፍል ሁለት] [ክፍል ሦስት] [ክፍል አራትና አምስት] [ክፍል ስድስት] [ክፍል ሰባትና ስምንት] [ክፍል ዘጠኝ] [ክፍል አስር]

M. Rafiqul-Haqq and P. Newton

ትርጉምና ቅንብር በአዘጋጁ

መግቢያ

የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ የሴቶችን ቦታ በእስላም ንፁህ ትምህርት ውስጥ ለመመልት ነው፡፡ ሁሉም ሙስሊም ወይንም ሁሉም የሙስሊም አገሮች ይህንን ትምህርት እንደማይከተሉት ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ትምህርቶች የመጡት ከሁለቱም ማለትም ከቁርአንም ከሐዲትም ላይ ነው፡፡ ሐዲት ‹የመሐመድ ልማድ ነው› ማለትም የመሐመድ ስራዎችና ንግግሮች ታሪኮች ነው፡፡ ይህ ሐዲት፡

‹በሰዎች ልጆች የሃይማኖት ሕይወት ምስረታና ፍፁምነትን በማግኘት ላይ ከቁርአን ጋር ጎን ለጎን በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በእርግጥ ከቁርአን ላይ ሐዲት ቢቀነስ፣ በየዕለቱ የሚሆነው የሰው ስራ ላይ በአብዛኛው ምንም የማይታወቅ ሆኖ ይቀራል› Mishkat al-Masabih, English translation, Book 1, Introduction: Qur'an and Hadith, p.3፡፡

ጃላል-ዑድ-ዲን አስ-ሱዩቲ የተባለው ተንታኝ የገለጠው ሐዲት፡ ‹የቁርአን አብራሪና የቁርአን መግለጫ ነው› Itqan fi 'Ulum al-Qur'an, Vol.II, p.182. በማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ቁርአንን ለመግለጥ ሁሉም ትንተናዎች የሚመሰረቱት በሐዲት ላይ የሚሆነው፡፡ ተቀባይነት ያለው ሐዲት ደግሞ የሚታመነው፡

‹ከመገለጥ ያነሰ አይደለም፣ (ቁርአን ስለ መሐመድ እንደሚከተለው ይላልና) ‹‹ነቢያችሁ መሐመድ ... ከልብ ወለድ አይናገርም፡፡ እርሱ (ንግግሩ) የሚወረድ ራእይ እንጂ ሌላ አይደለም›› ቁርአን 53.3-4)፡፡ በቁርአንና በሐዲት መካከል ያለው ብቸኛው ልዩነት፣ የመጀመሪያው በገብርኤል በኩል በቀጥታ በውስጡ ካሉት ፊደላት ከአላህ መገለጡ ሲሆን የሁለተኛው ግን የተገለጠው ያለ ቃላትና ያለ ፊደላት መሆኑ ነው› Mishkat al-Masabih, the English translation, Book 1, the importance of the Qur'an and Hadith, p.2,3.፡፡

‹ስለዚህም ከቁርአን ቀጥሎ ሐዲት በእስልምና የማህበራዊና የግል ባህርይ ሕግ (በኩል) ሁለተኛው ምንጭ ነው፣ ምክንያቱም የቅዱሱ ነቢይ ትዕዛዛት በአማኞች ላይ ልክ እንደ አላህ ህግጋት ተፈፃሚዎች ናቸውና፡፡ ‹አላህና መልእክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእመናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልእክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጥ የኾነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ› ቁርአን 33.36፡፡ Sahih Muslim, Introduction to English translation, P. ii.፡፡

ሐዲት ልክ እንዳለ ተቀባይነት ሊኖረው ይገባል ‹ከሐዲት ልዩ ለሚሆነው (ነገር) እስከ ፀጉር ድረስ ሊተው ይገባል› Mishkat al-Masabih, the English translation, Book 1, the importance of the Qur'an and Hadith, p.5, Quoted from Malabudda Minhu, p.8፡፡

‹ስለዚህም አንድ ሙስሊም የሚታየው ለሕይወቱ መመሪያ የአንድ ቁርአንና የአንድ ሐዲት ኮፒ የሚያስፈልገው ሆኖ ነው› Mishkat al-Masabih, the English translation, Book 1, the importance of the Qur'an and Hadith, p.5, Quoted from Malabudda Minhu, p.2,3፡፡

የወንዶች የበላይነት

ቁርአን በሚከተለው ቁጥር ላይ የፆታዎችን ስራ ጅማሬ አንድነት ይገልጣል፡

‹ጌታቸውም እኔ ከእናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሠሪን ስራ አላጠፋም ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው በማለት ለነርሱ ልመናቸውን ተቀበለ፣ ...› (ቁርአን 3.195)፡፡ ‹እላንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአዳም) የፈጠራችሁን ከርስዋም መቀናጆዋን (ሔዋንን) የፈጠረውን ከነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶችን የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ፣ ...› (ቁርአን 4.1)፡፡

ከዚህ በላይ ባሉት ጥቅሶች ቁርአን የወንዶችናን የሴቶችን ስራዎች በእኩልነት ሲገልጥ፣ ወንዶችም ከሴቶች በአፈጣጠራቸው በጣም የተለያዩ መሆናቸውን ይገልጣል፡፡ ይሁን እንጂ ወንዶችና ሴቶች እንደ ሰው እኩል ዋጋ ያላቸው ተደርገው አይወሰዱም፡፡ በሚከተሉት ሁለት ጥቅሶች ውስጥ በጣም ግልጥ እንደሆነው፣ ወንዶች ከሴቶች በላይ እንዲያውም ከእነሱ በጣም የመጠቁ ናቸው፡-

‹የተፈቱ ሴቶችም ነፍሶቻቸውን (ከማግባት) ሦስትን ቁርእ ይጠብቁ በአላህና በመጨረሻውም ቀን የሚያምኑ ቢኾን አላህ በማሕፀኖቻቸው ውስጥ የፈጠረውን ሊደብቁ ለነርሱ አይፈቀድላቸውም ባሎቻቸውም በዚህ ውስጥ እርቅን ቢፈልጉ በመማለሳቸው ተገቢዎች ናቸው፣ ለነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም አኑዋኑዋር (በባሎቻቸው ላይ መብት) አላቸው ለወንዶችም (ጣጣቸውን ስለሚሸከሙ) በነሱ ላይ ብልጫ አላቸው፣ አላህም አሸናፊም ጥበበኛ ነው› (ቁርአን 2.228) እና ‹ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፣ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡ መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች፣ አላህ ባስጠበቀው ነገር ሩቅን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ እነዚያንም ማመጣቸውን የምትፈሩትን ገሥጹዋቸው በመኝታዎችም ተለዩአቸው (ሳካ ሳታደርሱ) ምቱዋቸው፡፡ ቢታዘዙዋችሁም (ለመጨቆን) በነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ አላህ የበላይ ታላቅ ነውና› (ቁርአን 4.34)፡፡

ታዋቂው ተንታኝ ኢብን ካቲር ቁርአን 4.34 ላይ ትንተና ሲያደርግ የተናገረው፡

‹ወንዶች ከሴቶች የበለጡ ናቸው እና ወንድ ከሴት የተሻለ ነው› በማለት ነው፡፡ Ibn-Kathir, commenting on Q. 4:34.፡፡ ሌሎች ተንታኞችም፣ እንደ ራዚ፣ ባይዳዊ፣ ዛማክሻሪ እና ታባሪም ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው፡፡

ራዚ ደግሞ ቁርአን 4.11 ሲተነትን እንዲህ ነው ያለው፡

‹(የወንዶች ድርሻ የሁለት ሴቶች ድርሻ ያህል ነው)፡፡ ወንድ በተፈጥሮው ከሴት ይልቅ የተሻለና ፍፁም ነው፡፡ እንዲሁም በሃይማኖት በኩል፣ ማለትም ለመፍረድ (ፈራጅ ለመሆን) ብቁ በመሆን፣ ለአምልኮ መሪነት ብቁ በመሆኑ ነው፡፡ እንዲሁም የአንድ ወንድ ምስክርነት ከሴት ሁለት እጥፍ የበለጠ ነው፡፡ ስለዚህም ትልቅ ሃላፊነቶች የተሰጠው ማንም ቢኖር የተያያዘ ትልቅ ዕድል ሊሰጠው ይገባል፡፡ ሴት በእውቀት ጎደሎ በመሆኗ እንዲሁም ትልቅ ምኞት ስላላት፣ ለእርሷ ብዙ ገንዘብ ቢሰጣት የሚከተለው ብዙ ክስረት (ጥፋት) ነው፡፡ Razi commenting on the Q. 4:11. እንዲሁም ደግሞ በዚህ ላይ ራዚ የጨመረው፡ ‹በቁርአን 4.11 በመጀመሪያ የተጠቀሰው ወንድ ነው፤ ምክንያቱም ወንድ ከሴት በጣም የተሻለ ስለሆነ ነው› Razi commenting on the Q. 4:11፡፡ በራዚ ትንተና መሠረት የእንደዚህ ዓይነቱ የወንዶች የበላይነት በወንዶች የተፈጥሮ የበላይነት ነው፡፡ ይህም ‹በእውቀት እና በኃይል ነው ምክንያቱም ወንድ ለሚስቱ ጥሎሽን ስለሚሰጥና በእርሷም ላይ ገንዘብን ስለሚያወጣ ነው› Razi commenting on the Q. 4:34፡፡

አንድ ዘመናዊ ጸሐፊ ደግሞ ያለፈውን ጥቅስ በተመለከተ የሚከተለውን ተናግሯል፡

‹እግዚአብሔር የወንድን የበላይነት በሴት ላይ የመሰረተው ከላይ ባለው (ቁርአን 4.34) ጥቅስ መሰረት ነው፣ ማለትም ሴት ከወንድ ጋር እኩል መሆኗን የሚከለክለው ነው፡፡ ምክንያቱም እዚህ ነጥብ ላይ ወንድ ከሴት በላይ ነው፣ በእውቀቱ፣ በከፍተኛ ችሎታው፣ የማስተዳደር ችሎታ ስላለው እና በሴት ላይም ወጪን ስለሚያወጣ ነው› Tuffaha, Ahmad Zaky, Al-Mar'ah wal- Islam, Dar al-Kitab al-Lubnani, Beirut, first edition, 1985, p.36.፡፡   

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ

ቁርአን ወንዶች በተፈጥሮ ከሴቶች በላይ መሆናቸውን የተናገረባቸው ክፍሎችና ልዩ ልዩ የእስልምና ሊቃውንት በእነዚህ የቁርአን ክፍሎች ላይ የሰጡትን ትንተና ከላይ ባለው ጽሑፍ ውስጥ ሰፍረዋል፡፡

የክርስትያኖች አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለወንዶች ከፍ ያለ ቦታ ለሴቶች ደግሞ ዝቅተኛ ቦታን አይሰጥም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ወንዶችም ሴቶችም ከፆታ ልዩነት ባሻገር በተፈጥሮ እኩል እንደሆኑ፣ እኩል ኃጢአተኞች እንደሆኑ፣ አንድ ዓይነት በሆነ የእግዚአብሔር የማዳን መንገድ በጌታ በኢየሱስ በማመን እኩል ሊድኑ እንደሚችሉ በገልጥ ይናገራል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ አቀራረብ ለአስተዋይ አዕምሮ ስሜት የሚሰጥ፣ ሎጂካል፣ እና ለሕይወት እውነታ ታማኝነት ያለው ነው፡፡ የዚህ ድረ ገፅ አዘጋጆችም ጥማትና ፀሎት አንባቢዎች ይህንን እውነት እንዲገነዘቡትና ወደ እውነቱ እንዲመጡ ነው፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ከጸሐፊው ከእግዚአብሔር ጋር የምትታቀረቁበትን መንገድ አስተውሉ ጌታም በፀጋውና በኃይሉ በፍቅሩም ይርዳችሁ አሜን፡፡

ወደ ክፍል ሁለት ይቀጥሉ።

የትርጉም ምንጭ:  The Place of Women in Pure Islam  

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ